ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር በድርጅቱ ምስረታ ሂደት የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች እውቅና ሰጠ፡፡

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር በድርጅቱ ምስረታ ሂደት የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች እውቅና ሰጠ፡፡
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር በድርጅቱ ምስረታ ሂደት የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች እውቅና ሰጠ፡፡
ማህበሩ ባለፈው ጥር ወር የምስረታ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድና ከፌደራል ኅብረት ስራ ኮሚሽን እውቅና በማግኘት ነው እየሰራ ያለው፡፡
ሚያዝያ 24/2018 ዓ.ም በቶሊፕ ኦሎምፒያ ሆቴል ልዩ ሼር ሽያጭ ፕሮግራም ሲያካሂድ በዚህ ፕሮግራም ላይም ለምስረታ ሂደት ውጤታማነት የላቀ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ግለሰቦች እውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡
ሽልማቱን የሰጡት የማኅበሩ የስራ አመራር ሰብሳቢ ዶክተር እስማኤል ሀሰን፣ ምክትል ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ገነት ወልዴና የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢው ኮሚሽነር ዘመነ አመሸ ናቸው፡፡
በ10 ሚሊየን ብር መነሻ ካፒታል ተመሰረተው ኢንፊኒቲ ከአዲስ አበባ ባለፈ ወልቂጤ እና ደሴ ከተሞችን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ቅርንጫፎችን እንደሚከፍትም ታውቋል፡፡
ማህበረሰቡን የቁጠባ ባህሉ እንዲያድግ በማድረግና ለውጥ የሚያመጡ የብድር አገልግሎቶችን በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ መሆኑንም ሽልማቱን ያበረከቱት የማኅበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ገልጸዋል፡፡
ኅብረት ለዘላቂ ልማት!
Chat With Us