ኢንፊኒቲ በወለድ አልባ የፋናንስ አገልግሎት (Interest Free Banking) ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

ኢንፊኒቲ በወለድ አልባ የፋናንስ አገልግሎት (Interest Free Banking) ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
ኢንፊኒቲ በወለድ አልባ የፋናንስ አገልግሎት (Interest Free Banking) ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
-----------
ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መ/ቁ/ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር ለማህበሩ ስራ አመራር፣ ማኔጅመንት እና ሰራተኞች በወለድ አልባ የፋናንስ አገልግሎት (Interest Free Banking) ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው በዋናነት ከሸሪዐ አሰራር ጋር የተስማማ እና ምቹ የወለድ አልባ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡
በስልጠናውም የኢንፊኒቲ ሂዳያ ምርቶች ማለትም በሙራባሃ፣ ዋዲዓ የድ ደማን፣ ዋድዓ የድ አማና፣ ኢጃራ፣ ሙዳይ ቁጠባ እና የልጆች ቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶች ቀልጣፋ እና ምቹ አገልግሎት መስጠት በሚያስችሉ አሰራሮች ዙሪያ ነው የተሰጠው፡፡
ኢንፊኒቲ ሂዳያ ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መ/ቁ/ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር የእስልምና እምነትን መሰረት በማድረግ የሸሪዓ ህግና ድንጋጌን ተከትሎ የተለያየ አገልግሎቶችን የሚሰጥበት ነው፡፡
ስልጠናውም የተቋሙን አመራርና ሰራተኞ በቂ ወለድ አልባ የፋይናንስ አሰራርን በማወቅ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እንደሚያግዛቸው ተጠቁሟል፡፡
ማኅበሩ ለልጆች ልዩ ትኩረት በመስጠት በቤተሰብም ሆነ በትምህርት ተቋማት የሀገር ተረካቢ ህጻናትን ታሳቢ በማድረግ እየሰራ መሆኑ በስልጠናው ላይ ተነስቷል፡፡
ኢንፊኒቲ የማኅረሰቡን የፋይናንስ ችግር በመቅረፍ አካታች እና ቀልጣፋ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት እየሰራ የሚገኝ ሀገራዊ ማኅበር ነው፡፡
ኅብረት ለዘላቂ ልማት!
Chat With Us