ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መ/ቁ/ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር ከአሌፍታቭ አማካሪ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ሁለቱ ተቋማት የሚሰሯቸውን ስራዎች በጋራ እና በመተባበር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በሚያስችሏቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይም ተስማምተዋል፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢንፊኒቲ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እስክንድር መኩሪያ እና የኤፍታቭ አማካሪ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር በየነ ሞገስ ናቸው፡፡
አሌፍታቭ አማካሪ እና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በተለይም በማማከርና ምርምር እንዲሁም በቴክኖሎጂ አቅርቦትና በተቋማዊ ለውጥ ስራዎች ዙሪያ የሚሰራ ተቋም ነው፡፡
ተቋሙ ከኢንፊኒቲ ጋር በመተባበር የተቋማዊ ለውጥ አምጭ ዘመናዊ አሰራሮችንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማቅረብ እጅና ጓንት ሆኖ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል፡፡
ኢንፊኒቲ በቅርቡ የተቋቋመ ሀገራዊ የቁጠባ እና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ሲሆን በተለያዩ ዘርፎች የቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶችን በመስጠት የማኅበረሰቡን የፋይናንስ ችግር በመቅረፍ ለኢኮኖሚ እድገት የሚሰራ የፋይናንስ ተቋም ነው፡፡
በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ያለው ኢንፊኒቲ ከአሌፍታቭ ጋር ተፈራረሙት ስምምነትም ተግባራዊ ካደረጋቸው ዘመናዊ አሰራርና የቴክኖሎጂ ውጤቶች በተጨማሮ ዘመናዊ አሰራሮችን ወደ ስራ ለማስገባት እንደሚረዳው ተገልጧል፡፡
ሁለቱ ተቋማትም በስምምነታቸው መሰረት ውጤት ለማምጣት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ በስምምነታቸው ወቅት ተጠቁሟል፡፡
ኅብረት ለዘላቂ ልማት!
ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መ/ቁ/ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር ከአሌፍታቭ አማካሪ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡