የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የ2019 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ዕቅድን በተመለከተ ከኅብረት ሥራ ማህበራት አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።
በዚህ ውይይትም የኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሠረታዊ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር የስራ አመራርና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡ ማኅበሩ በዚህ ሀገራዊና ማኅበራዊ ጥሪ ላይ የበኩሉን አሻራ ለማሳረፍና አርአያነቱን ለማሳየት እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡ ማኅበሩ በማኅበራዊ ልማት በተለይም የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በመጠገንና በመገንባት፣ የመዋዕለ ሕፃናት ግንባታዎችን በፋይናንስና በቁሳቁስ በመደገፍ ኃላፊነቱን ይወጣል፡፡
ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ተማሪዎች የደብተርና የትምህርት ቁሳቁስ በማቅረብ የበኩሉን እንደሚወጣም በውይይቱ ላይ ገልጿል፡፡
ኢንፊኒቲ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር ላይ በንቃት በመሳተፍ እና በደም ልገሳ ንቅናቄ ተሳታፊ እንደሚሆንም ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ወጣቶችን በማነቃቃት፣ ስለ ኅብረት ሥራ፣ ስለ ቁጠባ ባህልና ተያያዥ ጉዳዮች ሥልጠናዎችን በመስጠት ኃገራዊ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ እየገለጸ ሁሉም አመራርና ሰራተኛ እንዲሁም መላው ማኅበረሰብ በዚህ ሀገራዊ ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆንም ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ኅብረት ለዘላቂ ልማት!
ኢንፊኒቲ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሀገራዊ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አስታወቀ፡፡