ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ስራ ማህበር በቻይና አፍሪካ ኢንተርፕረነርስ ጉባኤ ተሣተፈ።

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ስራ ማህበር በቻይና አፍሪካ ኢንተርፕረነርስ ጉባኤ ተሣተፈ።
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ስራ ማህበር በቻይና አፍሪካ ኢንተርፕረነርስ ጉባኤ ተሣተፈ። በአዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት ማንዴላ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ ታላቅ ጉባኤ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀስላሴን ጨምሮ ባለሥልጣናት፣ የአፍሪካ ህብረት መሪዎችና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በጉባኤውም ዋና ሥራ አ ሥፈጻሚ አቶ እሥክንድር መኩሪያ እና ምክትል ሥራ አሥፈጻሚና የቢዝነስ ልማት ዳይሬክተር አቶ ምሥጋናው አየለ የኀብረት ሥራ ማህበሩን በመወከል ተገኝተዋል። ጉባኤው በኢትዮጵያ እና በቻይና ኩባንያዎች መካከል የተሻለ ግንኙነት እንዲኖር ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ይታመናል። የኢንፊኒቲ የሥራ ኃላፊዎችም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል ኢንፊኒቲ በተያዘው በጀት ዓመት ከፌደራል ኀብረት ሥራ ኮሚሽን እውቅና የተሠጠውና በአጭር ጊዜ ውጤት እያሥመዘገበ የሚገኝ ሀገራዊ የፋይናንስ ተቋም ነው።
Chat With Us